ከዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፤ እስራኤላውያን ወደ አገሪቱ ለመግባት እየገፉ በሄዱ መጠን ጌታ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያባረራቸው አሕዛብ ይፈጽሙት የነበረውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ የይሁዳም ሕዝብ ይፈጽመው ነበር።
ዘሌዋውያን 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ በፊት የነበሩ የምድሪቱ ሰዎች ይህን ርኩሰት ሁሉ አድርገዋልና፥ ስለዚህ ምድሪቱ ረክሳለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ በፊት የነበሩት የምድሪቱ ኗሪዎች እነዚህን ርኲሰቶች ሁሉ ስለ ፈጸሙ ምድሪቱን አርክሰዋታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ በፊት የነበሩት የሀገሩ ልጆች ይህን ርኵሰት ሁሉ ሠርተዋልና፥ ምድሪቱንም አርክሰዋታልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ በፊት የነበሩ የአገሩ ልጆች ይህን ርኵሰት ሁሉ ሠርተዋልና፥ |
ከዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፤ እስራኤላውያን ወደ አገሪቱ ለመግባት እየገፉ በሄዱ መጠን ጌታ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያባረራቸው አሕዛብ ይፈጽሙት የነበረውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ የይሁዳም ሕዝብ ይፈጽመው ነበር።
የእስራኤልንም ነገሥታት መጥፎ አርአያነት ተከተለ፤ የገዛ ልጁን እንኳ ሳይቀር ለጣዖቶች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ይህንንም የፈጸመው የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ አገር ለመግባት ወደ ፊት እየገፉ በመጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከዚያች ምድር ነቃቅሎ ያስወገዳቸው አሕዛብ ይሠሩት የነበረውን አጸያፊ ድርጊት በመከተል ነው።
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
ሰውም ከጎረቤቱ ሚስት ጋር ርኩሰትን አደረገ፥ ሌላውም የልጁን ሚስት በዝሙት አረከሰ፥ ሌላውም በአንቺ ውስጥ የአባቱን ልጅ፥ እኅቱን አዋረደ።
እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ እንደ ወይን ዘለላ ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እንዳለ እንደ በለስ በኵራት በበለስ ዛፍ ላይ ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ባዓል-ፌዖር መጡ፥ ለእፍረትም ነገር ራሳቸውን ለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥
ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እናንተም የአገሩም ተወላጅ በእናንተም መካከል የሚኖር እንግዳ ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ማናቸውንም ነገር አታድርጉ፤
አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ትሠራለህ።
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።