እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።
ዘሌዋውያን 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷ እኅትህ ነችና ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የአባትህ ሚስት፣ ለአባትህ ከወለደቻት ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እኅትህ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኅትህ ስለ ሆነች ከአባትህና ከእንጀራ እናትህ ልጅ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ከአባትህ የተወለደች እኅትህ ናት፤ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ። |
እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።
የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ፤ የእነርሱ ኃፍረተ ሥጋ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና።
የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በአገር ቤት ወይም በውጭ አገር የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።