ቅድስተ ቅዱሳን ተብሎ የሚጠራ አንድ ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፤ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር።
ዘሌዋውያን 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። |
ቅድስተ ቅዱሳን ተብሎ የሚጠራ አንድ ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፤ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር።
ካህናቱም የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማስገባት፥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደነበረው ወደ ስፍራው አመጡት።
አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ለትውልዳችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።
ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ለማስተሰረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላችኋል።” ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።
“በዚህ በሰባተኛው ወር አሥረኛው ቀን የማስተስረያ ቀን ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።”
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ነገር ግን እጅግ ቅዱስ ወደ ሆኑት ነገሮች በቀረቡ ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲህ አድርጉላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ እያንዳንዱንም ሰው በየተግባሩና በየሥራው ጫና ይመድቡት፤
ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሔር ክብርና ከኀይሉ የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ መቅደሱ መግባት አልቻለም።