ዘሌዋውያን 13:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለምጽ ደዌ የተያዘ ሰው ነው፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ካህኑ፦ በእርግጥ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌው በራሱ ላይ የሚገኝ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ደዌ አለበት፤ ርኩስም ነው፤ በራሱ ላይ ካለው ቍስል የተነሣም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ የሥጋ ደዌ በሽተኛ ሰው በመሆኑ የረከሰ ነውና የረከሰ መሆኑን ካህኑ ያውጅ፤ በሽታውም በራሱ ላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምጻም ሰው ነው፤ ርኩስ ነው፤ ካህኑ፦ በርግጥ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ደዌው በራሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምጻም ሰው ነው፤ ርኩስ ነው፤ ካህኑ፦ በእርግጥ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌው በራሱ ነው። |
ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ የደዌው እብጠት፥ በሰውነቱ ቆዳ ላይ የሆነ የለምጽ ደዌ መስሎ፥ በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ላይ ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቢሆን፥
“የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው የሚለብሳቸው ልብሶች የተቀደዱ ይሁኑ፥ የራሱም ጠጉር የተጐሳቈለ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ እያለ ይጩኽ።
ዓይንህ የታመመች ከሆነች ግን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማው እንዴት የበረታ ይሆን!