ዘሌዋውያን 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር ሁሉ አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም ከደሟ እስክትነጻ ድረስ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷም ወራት እስኪፈጸም ድረስ ማንኛውንም የተቀደሰ ነገር አትንካ፤ ወደ ቤተ መቅደስም አትግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በተጨማሪ ደምዋ እስከሚጠራ እስከ ሠላሳ ሦስት ቀን ድረስ የተቀደሰውን ማናቸውንም ነገር መንካት የለባትም፤ ይህ የመንጻትዋም ጊዜ እስከሚፈጸም ድረስ ወደ ተቀደሰው ድንኳን አትግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፤ ወደ መቅደስም አትግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤ የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ። |
ነገር ግን ሴት ልጅ ብትወልድ እንደ ወር አበባዋ ጊዜያት ሁለት ሳምንት ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስልሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።