ሰቈቃወ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስታችን ለመጻተኞች፣ ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርስታችን ለባዕዳን ተሰጠ፤ ቤታችን ሁሉ የባዕዳን መኖሪያ ሆኖአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስታችን ለሌላ፥ ቤቶቻችንም ለእንግዶች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። |
አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፥ በማታውቃትም ምድር ለጠላቶችህ ባርያ እንድትሆን አደርግሃለሁ፤ ለዘለዓለም የሚነድደውን እሳት በቁጣዬ አንድዳችኋልና።”
ሀብታቸው ይዘረፋል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።