እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
ሰቈቃወ 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣ የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጽዮን ተራራ ባድማ ስለ ሆነች፥ ቀበሮዎች ይመላለሱበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽዮን ተራራ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮዎችም ተመላልሰውባታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።
በጌታ ስም፦ ‘ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፥ ይህችም ከተማ ባድማና ሰው የማይኖርባ ትሆናለች’ ብለህ ስለምን ትንቢት ተናገርህ?” ብለው ያዙት። ሕዝቡም ሁሉ በጌታ ቤት ውስጥ በኤርምያስ ላይ ተሰበሰቡ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ራሳችሁ አይታችኋል፤ እነሆ፥ ዛሬ ባድማ ሆነዋል፥ የሚቀመጥባቸውም የለም።
“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።