ሰቈቃወ 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣ የማንም እጅ ሳይረዳት፣ በድንገት ከተገለበጠችው፣ ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት የማንም እጅ ሳያርፍበት በቅጽበት ከተገለበጠችው ከሰዶም ቅጣት የበለጠ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች፥ ከሰዶም ኀጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኀጢአት በዛች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች። |
በሕዝቡ ላይ የሚሆነው እንዲሁ ካህኑ ላይ ይሆናል፤ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በአስተዳዳሪው፥ በአገልጋይቱም የሚሆነው እንዲሁ በእመቤትዋ፥ በሸማቹ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በሻጩ፥ በአበዳሪው የሚሆነው እንዲሁ በተበዳሪው፥ በዕዳ አስከፋዩም የሚሆነው እንዲሁ በዕዳ ከፋዩ ይሆናል።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።