ሰቈቃወ 3:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምኬት። በቁጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ራስህን በቍጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ ያለ ርኅራኄም ገደልኸን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በቊጣ ተሞልተህ አሳደድከን ያለ ርኅራኄ ገደልከን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳምኬት። በቍጣህ ከደንኸን፤ አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፤ አልራራህልንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳምኬት። በቍጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም። |
ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።
ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።