ሰቈቃወ 3:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆነ ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆነው እርሱ በራሱ ፍላጎት በሰው ላይ ችግርንና ሐዘንን ስለማያመጣ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልቡ አልተቈጣምና፥ የሰውንም ልጆች አላሳዘነምና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም። |
ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም።
በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።