Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የሟቹ ሞት አልደሰትምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ማንም እንዲሞት አልሻምና፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ወደ እኔ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እኔ ማንም ሰው እንዲሞት አልፈልግም፤ ስለዚህ ሁላችሁም ከኃጢአታችሁ ተመልሳችሁ በሕይወት ኑሩ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የም​ዋ​ቹን ሞት አል​ፈ​ቅ​ድ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስለ​ዚህ በን​ስሓ ተመ​ለ​ሱና በሕ​ይ​ወት ኑሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:32
9 Referencias Cruzadas  

ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥ በኃይል ታላቅ ነው፥ በፍርድና በጽድቅም ሃብታም ነው፤ አይጨቁንምም።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።


ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ ጌታም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።


የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም።


በውኑ በኃጢአተኛው ሞት እደሰታለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ከመንገዱስ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለምን?


በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።”


እርሱም ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲመጡ ፈቃዱ የሆነ አምላክ ነው።


አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos