La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሰቈቃወ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ ምሬትንና ሐሞትን ዐስባለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።

Ver Capítulo



ሰቈቃወ 3:19
9 Referencias Cruzadas  

“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኃያል የተፈራኸውም አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛና በነገሥታቶቻችን በአለቆቻችንም በካህናቶቻችንም በነብዮቻችንም በአባቶቻችንም በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።


“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።


የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ ዳዊትን፥ መከራውንም ሁሉ አስታውስ፥


አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ፊትህን ትሰውራለህ? እስከ መቼስ ቁጣህ እንደ እሳት ይነድዳል?


ለዳዊት በእውነት የማልህ፥ አቤቱ፥ የቀድሞ ጽኑ ፍቅርህ ወዴት ነው?


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? ጌታን ስለ በደልን አምላካችን ጌታ አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።


ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ።


ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ።