እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
ሰቈቃወ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶቿን ቅጥሮች፣ ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በዓመት በዓል ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤት በኀይል ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶችዋን ቅጽሮች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በበዓላት ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከፍተኛ ድምፅ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛይ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ጣለ፤ መቅደሱንም ጠላው፤ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ድምፃቸውን በዕልልታ አሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
‘የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣርያ እመልሳለሁ፥ እነርሱንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ።
“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል’ ብሎ ተናገረ።
ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፥ እኔንም ለማስቈጣት በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ካጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል።
የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች።
አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም።