ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ሰቈቃወ 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በበዓል ቀን ለግብዣ እንደምትጠራ፣ ሽብርን ከየአቅጣጫው በእኔ ላይ ጠራህ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ማንም አላመለጠም ወይም አልተረፈም፤ የተንከባከብኋቸውንና ያሳደግኋቸውን፣ ጠላቴ አጠፋብኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበዓል ቀን ይመስል ጠላቶቼን ከየቦታው ጋብዘሃል፤ በቊጣህ ቀን አንድም ያመለጠ ወይም በሕይወት የተረፈ የለም፤ ወልጄ ያሳደግኋቸውን ጠላቴ ፈጃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታው። የሚያሳድዱኝን እንደ በዓል ቀን ከዙሪያዬ ጠራ፥ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፤ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው። |
ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለምን መታኸን? ፈውስስ ስለምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።
በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከመንቈር ውስጥ ፈታው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ “ጌታ ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።
ከዚህ በኋላ፥ ይላል ጌታ፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህችም ከተማ የቀሩትን፥ አገልጋዮቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።’
አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ትሩፍ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ልጅንና ሕፃንን ከእናንተ ለማጥፋት ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።