በኢየሩሳሌም በአምላካችን ፊት ለሚያገለግሉ ካህናት የተለየውን፥ ከሕዝቡ አንድም ሰው በእጁ ሊነካቸው የማይፈቀድለትን የእህሉን በኵራትና የወይኑንና የዘይቱን አስራት ሊበሉ ወስነዋል።
የእህላቸውን መጀመሪያና የወይናቸውን ዐሥራት በፈጣሪያችን ፊት በኢየሩሳሌም ለሚቆሙ ለካህናት የለዩትን፥ ከሕዝቡም ላንድ ሰው ስንኳ በእጃቸው መዳሰስ የማይገባቸውን ይህን ዘይቱንም ሊበሉ አስበዋልና፥