መሳፍንት 8:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ በዓሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በዓሊምም አምላክ ይሆናቸው ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ በኣሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፥ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ። |
ኢያሱ በኖረበት ዘመን ሁሉ፥ ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የጌታን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ፥ እስራኤል ጌታን አገለገሉ።
እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥
ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ተው፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ ጌታንም አስቈጡት፤
እስራኤላውያን ግን ሌሎችን አማልክት ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንቶታቸውን አልሰሙም። አባቶቻቸው ጌታን በመታዘዘ በሄዱበት መንገድ ሳይሆን፥ አባቶቻቸው የጌታን ሕግ በመከተል ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ።
መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፥ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።
ጌዴዎን በወርቁ ኤፉድ ሠራ፤ በተወለደበትም ከተማ በዖፍራ አኖረው። እስራኤልም በሙሉ ኤፉዱን በማምለክ ስላመነዘሩ፥ ኤፉዱ ለጌዴዎንና ለቤተ ሰቡ ወጥመድ ሆነ።