Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ተው፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ ጌታንም አስቈጡት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም። እግዚአብሔርንም አስቈጡት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ፤ በዚህም ፈንታ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን የውሸት አማልክትን ማገልገል ጀመሩ፤ ለእነርሱም በመስገድ እግዚአብሔርን አስቈጡት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ቸ​ውን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዉ፤ ሌሎ​ች​ንም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፥ እግዚአብሔርንም አስቈጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 2:12
21 Referencias Cruzadas  

አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ ‘የአባቶቻቸው አምላክ ጌታ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ትተዉ፥


ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”


የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከጌታ ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ቤተሰብም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መርዘኛና መራራ የሆነ ፍሬ የሚያበቅል አይገኝባችሁ።


በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።


አዲሶች አማልክትን መረጡ፥ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበሮች ሆነ፥ በአርባ ሺህ በእስራኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አልታየም።


ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”


“ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፥ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፥ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፥ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።


ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤


ጌታም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብፃውያን፥ አሞራውያን፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥


በኰረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቈጡት፥ በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት።


ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።


ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።


በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።


እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤


ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ።


“ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ ከረከሳችሁ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በጌታ በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከሠራችሁ፥


በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios