መሳፍንት 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዜባሕና ጻልሙናም፥ “የሰው ጉልበቱ እንደ ሰውነቱ መጠን ነውና፥ አንተው ራስህ ግደለን አሉት፤” ጌዴዎንም ተነሥቶ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበሩትንም ጌጦች ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛብሄልና ስልማናም፣ “የሰው ጕልበቱ እንደ ሰውነቱ መጠን ነውና አንተው ራስህ ግደለን” አሉት፤ ጌዴዎንም ተነሥቶ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው ዐንገት ላይ የነበሩትንም ጌጦች ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዜባሕና ጻልሙናዕ ጌዴዎንን “በል እንግዲህ አንተው ራስህ ግደለን፤ የሰው ኀይሉ እንደ ሰውነቱ ነው” አሉት፤ ስለዚህ ጌዴዎን እነርሱን ገድሎ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበረውን ጌጣጌጥ በሙሉ ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሄልና ስልማናም፥ “ኀይልህ እንደ ጐልማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን” አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፤ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሄልና ስልማናም፦ የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፥ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ። |
ሌሎቹን ጌጣ ጌጦች ይኸውም የአንገት ሐብሉን ከነእንጥልጥሉ፥ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው አንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጉትቻ ክብደት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ።
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፥ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።