መሳፍንት 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ማረከ፤ መረመረውም፤ ወጣቱም የሰባ ሰባት የሱኮት ሹማምንትና የከተማይቱንም አለቆች ስም ጻፈለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ማረከ፤ መረመረውም፤ ወጣቱም የሰባ ሰባት የሱኮት ሹማምትና የከተማዪቱንም አለቆች ስም ጻፈለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሱኮትም ሰዎች አንዱን ወጣት ይዞ መረመረው፤ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች የነበሩትን የሰባ ሰባት ሰዎችን ስም ዝርዝር ጽፎ ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሱኮትም ሰዎች አንድ ብላቴና ይዞ መረመረው፤ እርሱም ሰባ ሰባቱን የሱኮትን አለቆችና ሽማግሌዎችን አስቈጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሱኮትም ሰዎች አንድ ብላቴና ይዞ ጠየቀው፥ እርሱም የሱኮትን አለቆችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች ጻፈለት። |
ከዚያም ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ለደከሙት ሰዎችህ እንጀራ እንሰጥ ዘንድ ዜባሕና ጻልሙና በእጅህ ገብተዋልን’ በማለት ያላገጣችሁብኝ ዜባሕና ጻልሙና እነዚሁላችሁ።”