መሳፍንት 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሠራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሰራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጌዴዎን በበረሓው መንገድ አድርጎ በኖባሕና በዮግበሃ ምሥራቅ በኩል ወጣና የጠላት ሠራዊት ሳያስበው በመዝናናት ላይ እያለ አደጋ ጣለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም በድንኳን የሚኖሩ ሰዎች ባሉበት መንገድ በኖቤትና በዮግቤል በምሥራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራዊቱም ተዘልሎ ሳለ አጠፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም የድንኳን ተቀማጮች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ በምሥራቅ በኩል ወጣ፥ ሠራዊቱም ተዘልሎ ነበርና ሠራዊቱን መታ። |
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፥ በሰላምና ያለ ስጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሏት።
በዚህ ጊዜ ዜባሕና ጻልሙና ዐሥራ አምስት ሺህ ከሆነ ሠራዊታቸው ጋር ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺህ ሰይፍ ታጣቂ ሠራዊት የተረፈው ነበር።
ከዚያም ሳሙኤል፥ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን?” በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።
ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፥ እነሆ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፥ ይጠጡና ይዘፍኑ፥ ይጨፍሩም ነበር።