መሳፍንት 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድያማውያን እስራኤላውያንን ችግር ላይ ስለጣሏቸው፥ ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድያማውያን እስራኤላውያንን ችግር ላይ ስለ ጣሏቸው፣ ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምድያምም ፊት የተነሣ እስራኤል እጅግ ተቸገሩ፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድያምም የተነሣ እስራኤል እጅግ ተጠቁ፥ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። |
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትተማመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደመስሳሉ።
ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”
እስራኤላውያን እንደገና ወደ ጌታ ጮኹ፤ ጌታም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ፥ ግራኙን፥ ኤሁድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።