La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! ከኤዶም ተራራ በተነሣህ ጊዜ፥ በኤዶምም ምድር ላይ በተራመድህ ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያት ዝናብን አዘነቡ፤ አዎ! ውሃ ከደመናዎች ወደታች ጐረፈ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ! ከሴ​ይር በወ​ጣህ ጊዜ፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ሜዳ በተ​ራ​መ​ድህ ጊዜ፥ ምድ​ሪቱ ተና​ወ​ጠች፤ ሰማ​ያ​ትም ጠልን አን​ጠ​ባ​ጠቡ፤ ደመ​ና​ትም ደግሞ ውኃን አን​ጠ​ባ​ጠቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 5:4
13 Referencias Cruzadas  

እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት


ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ።


ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ።


ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠባጠቡ።


አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፥ ጥልቆችም ተነዋወጡ።


ደመኖች ውሃን አዘነቡ፥ ደመኖች ድምፅን ሰጡ፥ ፍላጾችህም በየአቅጣጫው ወጡ።


ከዘለዓለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።


ተራሮች በሥሩ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆዎችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ ከቁልቁለት እንደሚወርድ ውኃ፥ ይሰነጠቃሉ።


እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ።


ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።