መሳፍንት 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሥታት መጡ፥ ተዋጉም፥ በዚያ ጊዜ በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፥ የብር ዘረፋም አልወሰዱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጊዶ ውሃ አጠገብ በታዕናክ፥ ነገሥታቱ መጥተው ተዋጉ፤ ከዚያም የከነዓንን ነገሥታት ተዋጉ፤ የብር ምርኮ አላገኙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ በዚያ ጊዜ በመጌዶ ውኆች አጠገብ በቶናሕ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፤ በቅሚያም ብርን አልወሰዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሥታት መጡ፥ ተዋጉም፥ በዚያ ጊዜ በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፥ የብር ዘረፋም አልወሰዱም። |
በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፦ የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፥ እንዲሁም በቤት ሻን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ፥ በጻርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተ ደቡብ ያለው ግዛት፥ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅመዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ።
በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
ኢዮስያስ ግን ማንነቱን ሸሽጎ ለመዋጋት ወጣ እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በጌታም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፥ በመጊዶም ሸለቆ ለመዋጋት መጣ።
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።
የምናሴ ነገድ ግን በቤትሳን፥ በታዕናክ፥ በዶር፥ በይብለዓም፥ በመጊዶንና በየአካባቢያቸው ያሉት መንደሮች ነዋሪውን ሕዝብ ስላላስወጡ፥ ከነዓናውያን ኑሮአቸውን በዚያው ለማድረግ ወሰኑ።
“ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጉርጉር ልብስ።”