መሳፍንት 3:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ናዖድ ቀረብ ብሎ፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ንጉሡ በጣራው ላይ ባለው ነፋሻ ክፍል ለብቻው ተቀምጦ ሳለ፥ ኤሁድ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “ከእግዚአብሔር ለአንተ የተላከ መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ብድግ ብሎ ቆመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዖድም ወደ እርሱ ቀረበ፥ እርሱም በሰገነት ቤት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፦ የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ አለ። ከዙፋኑም ተነሣ። |
የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?
እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ።