መሳፍንት 19:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዋ በጠዋት ተነሥቶ በሩን በመክፈት መንገዱን ለመቀጠል ሲወጣ፥ ቁባተ እጅዋን ከደጃፉ መድረክ ላይ እንደ ዘረጋች ከቤቱ በራፍ ላይ ተዘርራ ወድቃ አገኛት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዋ በጧት ተነሥቶ በሩን በመክፈት መንገዱን ለመቀጠል ሲወጣ፣ ቁባቱ እጇን ከደጃፉ መድረክ ላይ እንደ ዘረጋች ከቤቱ በራፍ ላይ ተዘርራ ወድቃ አገኛት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ጧት ባልየው ጒዞውን ለመቀጠል በሩን ሲከፍት ቊባቱ እጅዋን ወደ በሩ እንደ ዘረጋች በቤቱ ፊት ለፊት ወድቃ አገኛትና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፤ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፤ እነሆም፥ ዕቅብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆችዋም በመድረኩ ላይ ወድቀው አገኛት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዋም ማለዳ ተነሣ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፥ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፥ እነሆም ቁባቲቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ወድቃ፥ እጅዋም በመድረክ ላይ ነበረ። |