መሳፍንት 19:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ሌዋዊውም፥ “በይ ተነሺና እንሂድ” አላት፤ ነገር ግን መልስ አልነበረም። ከዚያም በአህያው ላይ ከጫናት በኋላ ወደ ቤቱ ጉዞውን ቀጠለ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ሌዋዊውም፣ “በዪ ተነሺና እንሂድ” አላት፤ ነገር ግን መልስ አልነበረም። ከዚያም በአህያው ላይ ከጫናት በኋላ ወደ ቤቱ ጕዞውን ቀጠለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 “ተነሽ እንሂድ!” አላት፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኘም፤ ከዚህ በኋላ ሬሳዋን በአህያ ላይ ጭኖ ወደ ቤቱ ጒዞውን ቀጠለ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 እርሱም፥ “ተነሺ እንሂድ” አላት፤ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፤ በዚያ ጊዜም በአህያው ላይ ጫናት፤ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ተመለሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 እርሱም፦ ተነሺ፥ እንሂድ አላት፥ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፥ በዚያን ጊዜ በአህያው ላይ ጫናት፥ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ሄደ። Ver Capítulo |