La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ተቀምጠው ሳሉ በእርሻ ቦታ የቀን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሽማግሌ በአጠገባቸው አለፈ፤ ይህ ሰው አስቀድሞ ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የመጣ ሲሆን፥ አሁን ግን የሚኖረው በጊብዓ ነበር፤ በዚያ የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች ግን ከብንያም ነገድ የተወለዱ ናቸው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፥ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ነበረ በጊብዓም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፥ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:16
16 Referencias Cruzadas  

“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”


ሰው ወደ ተግባሩ፥ እስኪመሽም ድረስ ወደ ሥራው ይወጣል።


የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፥ ምስጉን ነህ፤ መልካምም ይሆንልሃል።


በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።


በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፥ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።


ሥራህን በውጭ አሰናዳ፥ ለራስህ በእርሻ ውስጥ አዘጋጀው፥ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።


ከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁ፥ ይደክሙባት ዘንድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣት ከባድ ጥረት ናት።


ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፥ ራስን ለመጉዳት በባለቤቱ ዘንድ የተቀመጠ ሀብት።


በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ርኩሰት እነርሱም እንዲሁ እጅግ ረከሱ፤ እርሱም በደላቸውን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።


የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።


እንዲሁም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ማንም ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበር።


በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።


ስለዚህም መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ የብንያም ነገድ ወደ ሆነችው ወደ ጊብዓ እንደ ደረሱም ፀሓይ ጠለቀች።


ለማደርም ወደዚያው ጎራ አሉ፤ ሄደውም በከተማይቱ አደባባይ ተቀመጡ፤ ሆኖም በቤቱ ለማሳደር ማንም አልተቀበላቸውም ነበር።


ሽማግሌው ቀና ብሎ መንገደኛውን በከተማይቱ አደባባይ ላይ ባየው ጊዜ፥ “ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለህ?” ሲል ጠየቀው።