መሳፍንት 16:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ደሊላ ሳምሶንን፥ “የብርታትህን ታላቅነት ምስጢርና ታስረህ በቊጥጥር ሥር የምትውለው እንዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ደሊላ ሳምሶንን፣ “የብርታትህን ታላቅነት ምስጢርና ታስረህ በቍጥጥር ሥር የምትውለው እንዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ደሊላ ሶምሶንን “ይህን ያኽል ብርቱ የሚያደርግህ ምን እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ፤ አንድ ሰው አንተን አስሮ ሊያደክምህ የሚችለው እንዴት ነው?” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሊላም ሶምሶንን፥ “ታላቅ ኀይልህ በምን እንደ ሆነ፥ በምንስ ብትታሰር እንደምትዋረድ እባክህ ንገረኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሊላም ሶምሶንን፦ ታላቅ ኃይልህ በምን እንደ ሆነ፥ እንድትዋረድስ የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው። ሳምሶን የጌታ ባሪያ |
ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።
የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፥ “እርሱን አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደሆነ እንዲያሳይሽ እስቲ አባብይው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት።