Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “ታላቅ ኀይ​ልህ በምን እንደ ሆነ፥ በም​ንስ ብት​ታ​ሰር እን​ደ​ምትዋ​ረድ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህም ደሊላ ሳምሶንን፣ “የብርታትህን ታላቅነት ምስጢርና ታስረህ በቍጥጥር ሥር የምትውለው እንዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህም ደሊላ ሳምሶንን፥ “የብርታትህን ታላቅነት ምስጢርና ታስረህ በቊጥጥር ሥር የምትውለው እንዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ደሊላ ሶምሶንን “ይህን ያኽል ብርቱ የሚያደርግህ ምን እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ፤ አንድ ሰው አንተን አስሮ ሊያደክምህ የሚችለው እንዴት ነው?” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ደሊላም ሶምሶንን፦ ታላቅ ኃይልህ በምን እንደ ሆነ፥ እንድትዋረድስ የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው። ሳምሶን የጌታ ባሪያ

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:6
12 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ቃል አራት ጊዜ ላኩ​ብኝ፤ እኔም እንደ ፊተ​ኛው ቃል መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?


የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።


የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።


በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።


ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፥ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


ሰባ​ቱ​ንም የበ​ዓል ቀን አለ​ቀ​ሰ​ች​በት፤ እር​ስ​ዋም ነዝ​ን​ዛ​ዋ​ለ​ችና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ነገ​ራት። ለሕ​ዝ​ብ​ዋም ልጆች ነገ​ረ​ቻ​ቸው።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ወደ እር​ስዋ ወጥ​ተው፥ “እር​ሱን አባ​ብ​ለሽ በእ​ርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እር​ሱን ለማ​ዋ​ረድ እና​ስ​ረው ዘንድ የም​ና​ሸ​ን​ፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ሺህ አንድ መቶ ብር እን​ሰ​ጥ​ሻ​ለን” አሉ​አት።


ሶም​ሶ​ንም፥ “በሰ​ባት ባል​ደ​ረቀ በር​ጥብ ጠፍር ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos