መሳፍንት 16:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፥ “እርሱን አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደሆነ እንዲያሳይሽ እስቲ አባብይው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፣ “እርሱን አስረን በቍጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደ ሆነ እንዲያሳይሽ እስኪ አባብዪው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ወደ እርስዋ ሄደው እንዲህ አሉአት፤ “ሶምሶንን አግባብተሽ ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘው ከምን እንደ ሆነና እንዴትስ አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማድረግ ልናሸንፈው እንደምንችል ጠይቂው፤ እያንዳንዳችንም አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር እንሰጥሻለን።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ወደ እርስዋ ወጥተው፥ “እርሱን አባብለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን” አሉአት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የፍልስጥኤማውያንም መኳንንት ወደ እርስዋ ወጥተው፦ እርሱን ሸንግለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኃይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛስ እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ እወቂ፥ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን አሉአት። Ver Capítulo |