መሳፍንት 16:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤተሰብ ሬሳውን ለማምጣት ወደዚያ ወረዱ፤ አምጥተውም የአባቱ የማኑሄ መቃብር ባለበት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ቀበሩት። ሳምሶን እስራኤልን ለሃያ ዓመት መሪ ሆኖ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤተ ሰብ ሬሳውን ለማምጣት ወደዚያ ወረዱ፤ አምጥተውም የአባቱ የማኑሄ መቃብር ባለበት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ቀበሩት። ሳምሶን በእስራኤል ላይ ሃያ ዓመት ፈራጅ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቹና የቀሩት ቤተሰቡ ሁሉ መጥተው አስከሬኑን ወሰዱት፤ ወስደውም በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት፤ ሶምሶን ኻያ ዓመት ሙሉ እስራኤልን መራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹም፥ የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘውም አመጡት፤ በሶሬሕና በኢስታሔል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት። እርሱም እስራኤልን ሃያ ዓመት ገዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹም የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፥ ይዘውም አመጡት፥ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት። እርሱም በእስራኤል ላይ ሀያ ዓመት ፈረደ። |
“ከፍልስጥኤማውያን ጋር አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኃይሉ ሲገፋው፥ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው፤ ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ።