Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 16:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 “ከፍልስጥኤማውያን ጋር አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኃይሉ ሲገፋው፥ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው፤ ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “ከፍልስጥኤማውያን ጋራ አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኀይሉ ሲገፋው፣ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው። ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “ሕይወቴ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ትለፍ!” ብሎ ጮኸ፤ በሙሉ ኀይሉም በገፋቸው ጊዜ ሕንጻው በፍልስጥኤም ገዢዎቹና እዚያ ባሉት ሁሉ ላይ ተደረመሰ፤ ሶምሶንም በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው ይልቅ በሞተበት ጊዜ የገደላቸው በዙ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ሶም​ሶ​ንም፥ “ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎ​ን​ብ​ሶም ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋ​ቸው፤ ቤቱም በው​ስጡ በነ​በ​ሩት በመ​ሳ​ፍ​ንቱ፥ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞ​ቱም የገ​ደ​ላ​ቸው ሙታን በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከገ​ደ​ላ​ቸው በዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሶምሶንም፦ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት አለ፥ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኃይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፥ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:30
21 Referencias Cruzadas  

በትሕትና ራሱን ዝቅ አደረገ፤ በዚህም የመስቀልን ሞት እንኳ በመቀበል እስከ ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።


ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ግን ያገኛታል።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ በመስቀሉ ድል በመንሣት እነርሱን በይፋ አጋለጣቸው።


ምክንያቱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለመፈጸም ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ለክርስተቶስ ሥራ ሲል ለሞት ተቃርቦ ነበርና።


ነገር ግን በእምነታችሁ በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቊርባን ብፈስስ ደስ ይለኛል፤ ከእናንተም ከሁላችሁ ጋር አብሬ ሐሤት አደርጋለሁ፤


ጳውሎስ ግን መልሶ “እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም፤” አለ።


ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።


ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።


እርሱ ብቻ ዓለቴና መድኃኒቴም ነው፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ በፍጹም አልታወክም።


መዓትስ ለኃጢአተኛ፥ መገለልስ ለሚበድሉ ሰዎች አይደለችምን?


የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?


“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።


ክፉኛ መታቸው፤ ከነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኢታም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ።


ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ።


ከዚያም ቤተ ጣዖቱን መካከል ላይ ደግፈው የያዙትን ሁለት ምሰሶዎች አንዱን በቀኙ፥ አንዱን በግራ እጁ አቅፎ በመያዝ፥


ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤተሰብ ሬሳውን ለማምጣት ወደዚያ ወረዱ፤ አምጥተውም የአባቱ የማኑሄ መቃብር ባለበት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ቀበሩት። ሳምሶን እስራኤልን ለሃያ ዓመት መሪ ሆኖ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios