ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።
መሳፍንት 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳም ሰዎች፥ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልና ስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳም ሰዎች፣ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልናስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ሰዎች “በእኛ ላይ አደጋ የምትጥሉት ስለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሶምሶንን ልንይዝና እስረኛ አድርገን ወስደን በእኛ ላይ ያደረገውን ሁሉ በእርሱም ላይ ልንፈጽምበት ነው” ሲሉ መለሱላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ሰዎች፦ በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድር ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል አሉ። |
ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።