መሳፍንት 11:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የጌታ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ፤ ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ። ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ዮፍታሔም በገለዓድና በምናሴ ግዛቶች መካከል አቋርጦ ሄደ፤ በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ አለፈ፤ ከዚያም ወደ ዐሞን ጒዞውን ቀጠለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፥ እርሱም ገለዓድንና ምናሴን አለፈ፥ በገለዓድም ያለውን ምጽጳን አለፈ፥ ከምጽጳም ወደ አሞን ልጆች አለፈ። |
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
ጌታም በደመናው ውስጥ ሆኖ ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አኖረ፤ መንፈሱም በእነርሱ ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተናገሩም።
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በጌታ ፊት ደገመው።
የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።