ይሁዳ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ፣ በዙሪያቸውም ያሉ ከተሞች ለሴሰኛነትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት በመቀጣት ለሚሠቃዩት ምሳሌ ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። |
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”
ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።
“ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።
ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም እርሱ ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል በሚመጣበት ጊዜ መከራን ለተቀበላችሁት ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል፤
ነገር ግን አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር በዚሁ ቃል፥ እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀው ይቆያሉ።