ኢያሱ 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ባረካቸው፥ እንዲሄዱም አሰናበታቸው፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱ መርቆ አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም መረቃቸው፤ አሰናበታቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፥ ወደ ቤታቸውም ሄዱ። |
የእስራኤል ወገን ለሆነው ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድ ቁራጭ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ ሰጠ፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም ወደየቤቱ ሄደ።
ዳዊትም ቤተሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ግን ልትቀበለው ወጣችና፥ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ራቁቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው።
በሚቀጥለውም ቀን ሰሎሞን ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ።
እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ብዙ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ “ቸሩ ጌታ ሆይ! ሁሉንም ሰው ይቅር በል፤
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፦ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት እንዲሆን ተሾሞአል፤
ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ተግባርና ሥርዓት ለሕዝቡ ገልጦ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በጌታ ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።
ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ “ለጌታ ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት ጌታ ዘር ይስጥህ” ብሎ ባረካቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።