Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፥ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም ኢያሱ መርቆ አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢያሱም ባረካቸው፥ እንዲሄዱም አሰናበታቸው፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ኢያ​ሱም መረ​ቃ​ቸው፤ አሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 22:6
18 Referencias Cruzadas  

ባረከውም፤ አብራም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፤


ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ።


ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው።


ዳዊትም የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ማሳረግ ከፈጸመ በኋላ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም መረቀ።


ለሕዝቡም ሁሉ ለእስራኤል ወገን ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ አንዳንድም የሥጋ ቁራጭ አንዳንድም የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ። ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።


ዳዊትም ቤተ ሰቡን ሊመርቅ ተመለሰ። የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ለመቀበል ወጣችና፦ ምናምንቴዎች እርቃናቸውን እንደሚገልጡ የእስራኤል ንጉሥ በባሪያዎቹ ቈነጃጅት ፊት እርቃኑን በመግለጡ ምንኛ የተከበረ ነው! አለችው።


በስምንተኛውም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነርሱም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔርም ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ተደስተው ሐሤትም አድርገው ወደ ስፍራቸው ሄዱ።


እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ።


ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆም አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።


ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም፦ እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።


እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።


ኢያሱም ባረከው፥ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።


ኢያሱም ሕዝቡን በእያንዳንዱ ወደ ርስቱ ሰደደ።


ሳሙኤልም የመንግሥቱን ወግ ነገረ፥ በመጽሐፍም ጻፈው በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው።


ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፥ ሁለቱም ሺህ በማክማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፥ አንዱም ሺህ በብንያም ጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ፥ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።


ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ ለእግዚአብሔር ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር ዘር ይስጥህ ብሎ ባረካቸው፥ እነርሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos