ኢያሱ 21:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጌርሶን ዝርያዎች ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌም ነገድ ጐሣዎችና ባሳን ውስጥ ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጌርሾን ጐሣ ከይሳኮር፥ ከአሴር፥ ከንፍታሌምና በባሳን ካለው ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ይዞታዎች ተከፍለው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው። |
ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።