በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።
ኢያሱ 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምጽጳ፥ ከፊራ፥ ሞጻ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምጽጳ፣ ከፊራ፣ አሞቂ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምጽጳ፥ ከፊራ፥ ሞጻ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማሴማ፥ ቤሮን፥ አሞቂ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምጽጳ፥ ከፊራ፥ አሞቂ፥ |
በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ፥ ባዕሻ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ ምጽጳንና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት።
እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
በምሥራቅና በምዕራብም ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞራዊውም፥ ወደ ኬጢያዊውም፥ ወደ ፌርዛዊውም፥ በተራራማውም አገር ወዳለው ወደ ኢያቡሳዊው፥ ከአርሞንዔምም በታች በምጽጳ ወዳለው ወደ ኤዊያዊው ላከ።
ዮፍታሔ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆ፤ ልጁ አታሞ እየደለቀች በመዝፈን ልትቀበለው ወጣች፤ እርሷም አንዲት ልጁ ብቻ ነበረች፤ ከእርሷ በቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም።
ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በጌታ ፊት ተሰበሰቡ።
እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።