La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 17:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ወረደ፤ በምናሴም ከተሞች መካከል ከወንዙ በደቡብ በኩል የሚገኙት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፤ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም በመቀጠል ድንበሩ በደቡብ በኩል ወደ ቃና ወንዝ ይደርሳል። በምናሴ ከተሞችም መካከል የኤፍሬም ከተሞች ነበሩ፤ ያም ሆኖ የምናሴ ድንበር የወንዙ ሰሜናዊ ክፍል ሲሆን፣ እስከ ባሕሩ ይዘልቃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ድንበሩም ከዚያ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርሳል፤ ከወንዙ በስተ ደቡብ የሚገኙት ከተሞች ምንም እንኳ በምናሴ ግዛት ክልል ውስጥ ቢሆኑ የኤፍሬም ይዞታዎች ነበሩ፤ የምናሴ ድንበር በሰሜን በኩል ከወንዙ እየተዋሰነ መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ቃራና ሸለ​ቆና ወደ ኢያ​ሪ​ያል ሸለቆ ይወ​ር​ዳል፤ የኤ​ፍ​ሬም ዕጣ የሆ​ነው ጤሬ​ሜ​ን​ቶስ የሚ​ባ​ለው ዛፍም በም​ናሴ ከተ​ሞች መካ​ከል አለ፤ የም​ና​ሴም ድን​በር በሰ​ሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ከወንዙ በደቡብ ወገን ወረደ፥ በምናሴም ከተሞች መካከል የነበሩት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፥ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 17:9
4 Referencias Cruzadas  

ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ድንበር እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ድንበር እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።


በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ ነበረ፥ ድንበሩም የባሕሩ ዳርቻ ነበረ፤ በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ።


ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መጨረሻውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤