La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ስለወረሱ፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ስለሆነ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምናሴ ነገድ ሴት ልጆች ከወንዶቹ ጋራ ርስት ተካፍለዋልና። የገለዓድ ምድር ግን ለቀሩት የምናሴ ዘሮች ተሰጠ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቶች ዘሮቹ እንደ ወንዶች ዘሮቹ የርስት ድርሻ ስለ ተቀበሉ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ዘሮች ተሰጠ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ናሴ ሴቶች ልጆች በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ የገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች ሆኖ​አ​ልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ተቀብለዋልና፥ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና።

Ver Capítulo



ኢያሱ 17:6
7 Referencias Cruzadas  

ከንፍታሌም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ምናሴ አንድ ድርሻ ይኖረዋል።


ሙሴም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት ሰጣቸው፤ ለምናሴም ልጆች ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው ድርሻቸው ይህ ነበረ።


ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥


የገለዓድም እኩሌታ፥ በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ድርሻቸው ሆነ።


በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ደረሰው፤


የምናሴም ግዛት ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ነበረ፤ ድንበሩም በቀኝ በኩል ወደ ዓይንታጱዋ ሰዎች አለፈ።


ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው ለእኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ ወገን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው ባሰናበታቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥