ኢያሱ 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ርስታቸው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም በምናሴ ርስት ክልል ውስጥ ያሉትንና ለኤፍሬማውያን የተሰጡትን ከተሞችና መንደሮችንም ይጨምራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር፥ ነው። |
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ሴኬምና መንደሮችዋ ጋዛና መንደሮችዋ ነበሩ፤
በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።
ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ወረደ፤ በምናሴም ከተሞች መካከል ከወንዙ በደቡብ በኩል የሚገኙት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፤ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።