ዮሐንስ 7:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፥ ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ መጽሐፍ አልተናገረምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጽሐፍ፣ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፣ ዳዊትም ከኖረበት ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሲሕ ከዳዊት ዘር እንደሚወለድና ከዳዊት ከተማ ከቤተልሔም እንደሚመጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎ የለምን?” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጽሐፍ ‘ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና ከዳዊት ከተማ ከቤተ ልሔም ይመጣል’ ይል የለምን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን?” አሉ። |
“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።
ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነው” ብሎ መለሰ።
ሳሙኤል ጌታ ያለውን ነገር አደረገ። ቤተልሔም እንደደረሰም፥ የከተማዪቱ ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡ፥ እነርሱም “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ብለው ጠየቁት።