Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 7:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 መጽ​ሐፍ ‘ክር​ስ​ቶስ ከዳ​ዊት ዘርና ከዳ​ዊት ከተማ ከቤተ ልሔም ይመ​ጣል’ ይል የለ​ምን?”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 መጽሐፍ፣ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፣ ዳዊትም ከኖረበት ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለምን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፥ ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ መጽሐፍ አልተናገረምን?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 መሲሕ ከዳዊት ዘር እንደሚወለድና ከዳዊት ከተማ ከቤተልሔም እንደሚመጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎ የለምን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:42
17 Referencias Cruzadas  

አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


እነርሱም “ ‘አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና’ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው” አሉት።


ዮሴ​ፍም ከገ​ሊላ አው​ራጃ ከና​ዝ​ሬት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ቤተ ልሔም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ዳዊት ከተማ ወጣ፤ እርሱ ከዳ​ዊት ሀገ​ርና ከዘ​መ​ዶ​ቹም ወገን ነበ​ርና።


“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


እነሆ፥ ዛሬ በዳ​ዊት ከተማ መድ​ኅን ተወ​ል​ዶ​ላ​ች​ኋል፤ ይኸ​ውም ቡሩክ ጌታ ክር​ስ​ቶስ ነው።


የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።


ከእ​ሴይ ሥር በትር ትወ​ጣ​ለች፤ አበ​ባም ከግ​ንዱ ይወ​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።


ሺህ ዓመት በፊ​ትህ እን​ዳ​ለ​ፈች እንደ ትና​ንት ቀን፥ እንደ ሌሊ​ትም ሰዓት ነውና።


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።


ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜስ ከወ​ዴት እንደ ሆነ ማንም አያ​ው​ቅም”።


ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።


ሳሙ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን አደ​ረገ፤ ወደ ቤተ ልሔ​ምም መጣ። የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በተ​ገ​ና​ኙት ጊዜ ደነ​ገጡ፥ “ነቢይ! የመ​ጣ​ኸው ለሰ​ላም ነውን?” አሉት።


የቤተ ልሔም አባት ሰል​ሞን፥ የቤት ጋዲር አባት ኦሪ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios