ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
ዮሐንስ 3:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ እንዲልቅ እኔ ግን እንዳንስ ያስፈልጋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ከፍ ከፍ ማለት ይገባዋል፤ እኔ ግን ዝቅ ዝቅ ማለት ይገባኛል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእርሱ ትበዛለች፤ የእኔ ግን ታንስ ዘንድ ይገባል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። |
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”