ዮሐንስ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርዱም ይህ ነው፥ ብርሃንም ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍርዱም ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ፍርዱም ይህ ነው፦ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ሆነ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዱም ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጥቶአልና፤ ሰውም ሥራው ክፉ ስለሆነ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን መርጦአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። |
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።