La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 19:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተሰቀለበትም ስፍራ የአትክልት ቦታ ነበረ፤ በአትክልቱም ቦታ ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታም የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልቱም ስፍራ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ ተሰቅሎ በነበረበት ቦታ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም የአትክልት ስፍራ ውስጥ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም በተ​ሰ​ቀ​ለ​በት ቦታ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ነበር፤ በዚያ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ውስ​ጥም በው​ስጡ ሰው ያል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት አዲስ መቃ​ብር ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 19:41
7 Referencias Cruzadas  

ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት።


መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ?


ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብሩ አኖረው፤ በመቃብሩ በር ላይ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።


አውርዶም በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው።


መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረና የአይሁድ የዝግጅት ቀን ስለ ነበረ ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።


ኢየሱስም “አንቺ ሴት! ስለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ፤” አለችው።