Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 19:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቶ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እነርሱም የኢየሱስን በድን ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋራ ከተልባ እግር በተሠራ ጨርቅ ከፈኑት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሁለቱ ሰዎች የኢየሱስን አስከሬን ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቶ ጋር በቀጭን ልብስ ከፈኑት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልምድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 19:40
9 Referencias Cruzadas  

ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።


ጐበዞችም ተነሥተው ከፈኑት፤ አውጥተውም ቀበሩት።


ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብር ሮጠ፤ በዚያም ዝቅ ብሎ ሲመለከት ቀጭን የሐር ልብስ ለብቻ ተቀምጦ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤቱ ሄደ።


እርሷ ይህን ሽቶ በሰውነቴ ላይ በማፍሰስ ለቀብሬ አደረገችው።


ዮሴፍም አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።


ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቶ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት።


እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።


ኢየሱስም “ለምቀበርበት ቀን እንድትጠብቀው ተውአት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios