አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ።
ዮሐንስ 19:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስቀሉንም ተሸክሞ የራስ ቅል ወደሚሉት ስፍራ፥ በዕብራይስጥም ጎልጎታ ወደ ተባለው ቦታ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የራሱን መስቀል ተሸክሞ በአራማይክ “ጎልጎታ” ተብሎ ወደሚጠራው “የራስ ቅል” ወደተባለው ቦታ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። |
አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ።
እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”
ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሽጥ፤ ለድኾችም ስጥ፤ በሰማይ የተከማቸ ሀብት ታገኛለህ፤ ከዚያ በኋላና፤ ተከተለኝም” አለው።
አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፥ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስቲ ከመስቀል ይውረድ።” ከእርሱ ጋር የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።
ከዚህ በኋላ፥ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤
ጲላጦስም ይህን ነገር ሰምቶ ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፤ በዕብራይስጥም ገበታ በተባለው “ጠፍጣፋ ድንጋይ” በሚሉት ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ።