ዮሐንስ 18:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በፋሲካ አንድ ሰው እንድፈታላችሁ ልማድ ሆኖአል፤ የአይሁድን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በፋሲካ አንድ እስረኛ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ ስለዚህ፣ ‘የአይሁድን ንጉሥ’ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እንደ ልማዳችሁ በፋሲካ በዓል ሁልጊዜ አንድ እስረኛ እፈታላችኋለሁ፤ ስለዚህ የአይሁድን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በየዓመቱ በፋሲካ በዓል ከእስረኞች አንድ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በፋሲካ አንድ ልፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?” አላቸው። |